ስለ አዲስ ሆም ፋይንደር

አዲስ ሆም ፋይንደር ለሪል ስቴቶችና ለቤት ገዥዎች ሞያዊ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ/ኩባንያው ቤት የመግዛትንና የመሸጥን ሂደት በማመቻቸት ግብይቱን ለሁሉም አካላት ቀላል ማድረግን አላማው አድርጎ የተመሰረተ ነው፡፡ ሪል ስቴቶች ንብረቶቻቸውን መሸጥ ሲቸግራቸውና ቤት ገዥዎች ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን ግራ ሲጋቡ በማየት አዲስ ሆም ፋይንደር ለቤት ገዥዎችና ሪል ስቴቶች መካከል ትክክለኛ ትስስር እንዲኖር በማስቻል እና የኢንዱስትሪው ግብይቱን ዘመናዊ በማድረግ አዲስ ታሪክ መፃፍን ግቡ አድርጎ የተነሳ ነው፡፡

ቤት መግዛት የረጂም ጊዜ መዋዕለ ነዋይን ማፍሰስ ማለት በመሆኑ ትክክለኛ ቤት መምረጥ የህይወት እጅግ ከባዱ ውሳኔ ነው፡፡ በመሆኑም አገልግሎታችን ለኢትጵያውያን ቤት ገዥዎች ቤት የመፈለግን ጫና በማቅለል ቤቴ ብለው ሊጠሩት የሚችሉትን ምርጥ ቤቶች ስናቀርብላቸው ታላቅ ክብር ይሰማናል!