115 ካሬ ባለ 3 መኝታ ክፍል አፓርታማ

ቅድመ ክፍያ 549,895.50 ብር

የቤት መግለጫ

እነኝህ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለ 3 መኝታ አፓርታማ ቤቶች የሚገኙት በመሃል አዲስ አበባ በሲ.ኤም.ሲ በመሆኑ በጣም ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡ የገበያ ማእከሎች፣ የእምነት ቦታዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች በቅርብ ርቀት ይገኛሉ፡፡ አብዛኞች እነኝህ አይነት ቤቶች የተሰሩት የገበያ ማዕከል ያለው አፓርታማ ላይ ነው፡፡ በአፓርታማው ላይ የሚገኙት የመጀመሪያዎቹ 3ቱ ወለሎች ለንግድ የሚሆኑ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወለሎች ደግሞ ለመኖሪያ የሚሆኑ ናቸው፡፡ እነኝህ ውብ ቤቶች የወለል ፕላን አማራጭ ያላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ወለል ፕላን ስፋቱ 24.6 ካሬ ሜትር የሆነ ሳሎን እና መመገቢያ ክፍል፣ ስፋቱ 15 ካሬ ሜትር የሆነ ዋና መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 12 ካሬ ሜትር የሆነ ሁለተኛ መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 8.7 ካሬ ሜትር የሆነ ሶስተኛ መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 6 ካሬ ሜትር የሆነ የሰራተኛ ክፍል እና ስፋቱ 10 ካሬ ሜትር የሆነ ማዕድ ቤት/ወጥ ቤት ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው የወለል ፕላን ደግሞ ስፋቱ 25.4 ካሬ ሜትር የሆነ ሳሎን እና መመገቢያ ክፍል፣ ስፋቱ 16.3 ካሬ ሜትር የሆነ ዋና መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 10 ካሬ ሜትር የሆነ ሁለተኛ መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 9.6 ካሬ ሜትር የሆነ ሶስተኛ መኝታ ክፍል፣ ስፋቱ 4.7 ካሬ ሜትር የሆነ የሰራተኛ/እቃ ክፍል እና ስፋቱ 10.7 ካሬ ሜትር የሆነ ሰፊ ማዕድ ቤት/ወጥ ቤት ያለው ነው።እንዲሁም ቤቶቹ ቨረንዳ እና 3 መታጠቢያ ክፍሎች አላቸው ።

በተጨማሪ

ለባቡር ጣቢያው አቅራቢያ/ቅርብ
አሳንሰር/ሊፍት
የቆሻሻ መጣያ ያለው

የቪዲዮ ጉብኝት

አካባቢ