109 ካሬ ባለ 3 መኝታ ክፍል አፓርታማ

ቅድመ ክፍያ 521,205.30 ብር

የቤት መግለጫ

እነኝህ ባለ 3 የመኝታ ክፍል ዘመናዊ ቤቶች ምቹ፣ ለእርሶና ለቤተሰብዎ የሚመጥኑ ብሎም በቂ መጠቅምያ ቦታ እንዲኖረዎት ተደርጎ የተሰሩ ናቸው፡፡ በሲ.ኤም.ሲ የሚገኙት እነኝህ ባለ 3 መኝታ ዘመናዊ አፓርታማ ቤቶች ገዥዎች በቀላሉ የሚመርጧቸው ሲሆኑ በእርሶ የበጀት አቅም ውስጥ ናቸው፡፡ እነዚህ ቤቶች ሁለት የተለያየ የወለል ፕላን ያላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ወለል ፕላን 30 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሳሎን እና መመገቢያ ክፍል፣ 14.2 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ዋና መኝታ ቤት፣ 9 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሁለተኛ መኝታ ቤት፣ 7 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሶስተኛ መኝታ ቤት እና 10 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ወጥ ቤት ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው የወለል ፕላን አማራጭ ተጨማሪ እቃ ቤት እና መታጠቢያ ክፍሎች ስላለው ከላይ ካለው ቤት በመጠኑ ይለያል፡፡ ሳሎን እና መመገቢያ ክፍሉ ወደ 25.4 ካሬ ሜትር፣ ዋናው መኝታ ክፍል 15.3 ካሬ ሜትር፣ ሁለተኛው መኝታ ክፍል 11.2 ካሬ ሜትር፣ ሶስተኛው መኝታ ክፍል 7.5 ካሬ ሜትር፣ እቃ ቤቱ 3 ካሬ ሜትር እና ማዕድ ቤቱ 10 ካሬ ሜትር ነው፡፡

በተጨማሪ

ለባቡር ጣቢያው አቅራቢያ/ቅርብ
አሳንሰር/ሊፍት
የቆሻሻ መጣያ ያለው

የቪዲዮ ጉብኝት

አካባቢ