145 ካሬ ባለ 3 መኝታ ክፍል አፓርታማ

ቅድመ ክፍያ 693,346.50 ብር

የቤት መግለጫ

እነዚህ ባለ 3 መኝታ ክፍል ቅንጡ ቤቶች እርሶና ቤተሰቦ ጥሩ የህይወት ትዝታ እንዲኖራችሁ ለማስቻል ታስቦ ሰፋ ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ቤቶቸ በሲ.ኤም.ሲ ብቻ የሚገኙ ሲሆን አንድ የወለል ፕላን ብቻ የቀረቡ ሲሆኑ ሁሉም መኝታ ክፍሎች እና ሳሎን በጣም የተዋበውን የመኖሪያ አካባቢ ጥሩ እይታ እንዲኖርዎ ታስበው የተሰሩ ናቸው፡፡ በዚህ የወለል ፕላን 35.7 ካሬ ሜትር የሆነ ሳሎን እና መመገቢያ ክፍል፣ ስፋቱ 20 ካሬ ሜትር የሆነ ዋና መኝታ ክፍል ፣ ስፋታቸው 17.5 ካሬ ሜትር የሆነ ሁለተኛ መኝታ ቤት እና 9 ካሬ ሜትር የሆነ ሶስተኛ መኝታ አላቸው ። በተጨማሪ ስፋቱ 5.6 ካሬ ሜትር የሆነ የሰራተኛ ክፍል እንዲሁም 3 መታጠቢያ ክፍሎች፣ሰፊ ቨረንዳና 10 ካሬ ሜትር ማዕድ ቤት/ወጥ ቤት አላቸው ፡፡

የቪዲዮ ጉብኝት

አካባቢ